በኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በብሪክስ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በብሪክስ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ነው
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2016 (ኢዜአ):- በፌደራል የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በኦስትሪያ ቪዬና እየተካሄደ ባለው የብሪክስ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
በስብሰባው ላይ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋና የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ተካፋይ ናቸው።
ስብሰባው የብሪክስ አባል አገራት በስፖርቱ ዘርፍ የሚስተዋሉ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን መከላከል በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።
ውይይቱ እስከ ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚቆይ ከፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።