ወደታችኛው የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ተጨማሪ ብስራት ከጉባ ተደምጧል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ወደታችኛው የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ተጨማሪ ብስራት ከጉባ ተደምጧል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 19/2016(ኢዜአ)፦ ወደታችኛው የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ተጨማሪ ብስራት ከጉባ ተደምጧል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የወንዝ ፍሰት ሳይስተጓጎል ከመቀጠሉም በተጨማሪ የግድቡ የውሃ ማስተንፈሻ በሮች ተከፍተው ተጨማሪ 2800 ሜኪ ውሃ በሰከንድ ማፍሰስ ጀምረዋል ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ፍሰትን በመቆጣጠር፣ የጎርፍ አደጋ ስጋትን በመቀነስ፣ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በተለይ በድርቅ ዘመን መጠኑ ያልዋዠቀ የውሃ አቅርቦት እንዲደርሳቸው ያደርጋል ሲሉም ገልጸዋል።
ይህ የተመዘነና የተመጣጠነ የውሃ ልቀት ግብርናን፣ የኃይል የማመንጨት ሥራን፣ በቀጠናው ያለ የሀብት አጠቃቀም ምጣኔን ለማጎልበት በእጅጉ ይጠቅማል ብለዋል።