በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የአምራች ኢንዱስትሪውን የኢኮኖሚ ድርሻ ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታማ ነበሩ - አቶ መላኩ አለበል - ኢዜአ አማርኛ
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የአምራች ኢንዱስትሪውን የኢኮኖሚ ድርሻ ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታማ ነበሩ - አቶ መላኩ አለበል

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የአምራች ኢንዱስትሪው በአገሪቱ ኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታማ እንደነበሩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ያተኮረ ውይይት በሀዋሳ ከተማ እያካሄደ ነው ።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፣ ሚኒስቴሩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የያዛቸውን ዕቅዶች ለማሳካት ውጤት የተገኘባቸውን ሥራዎችን አከናውኗል።
በተለይ አምራች ኢንዱስትሪው በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታማ እንደነበሩ አስታውቀዋል።
ገቢ ምርትን በመተካት፣ የወጪ ምርትን በማሳደግ፣ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሚፈለገውን ለውጥ እንዲያመጣ የተደረገው እንቅስቃሴ አመርቂ ውጤት እንደተመዘገበበትም አቶ መላኩ ተናግረዋል።
በዚህም ለቀጣይ ጊዜያት ስንቅ የሚሆኑ ተግባራት ተከናውነዋል ያሉት ሚኒስትሩ፣ በተያዘው በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ይሰራል ብለዋል።
በመድረኩ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሚኒስትር ዴኤታዎች እንዲሁም የክልሎች፣ የከተማ አስተዳደሮችና የተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም እየተሳተፉ ነው።
ከውይይቱ በኋላ ባለፈው በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት እውቅናና ሽልማት እንደሚበረከት ለማወቅ ተችሏል።