ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 18/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

የክልልና ከተማ አስተዳደር እስልምና ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ የምክር ቤቱ አባላት፣ ዑለማዎች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በጉባኤው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት ዓመታት ለሕዝበ ሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን ለአገር የሚጠቅሙ በርካታ ተግባራት መከናወኑን ተናግረዋል። 


 

በዛሬው ጉባኤ የ2015 የውጭ ኦዲት ሪፖርት፣ የ2016 የክንውን ሪፖርት፣ የ2016 የሐጅ ሪፖርትና  የ2017 የእቅድ ሪፖርት ላይ ውይይት እንደሚደረግ ገልጸዋል። 

ጉባኤው የተገኙ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እንዲሁም የተገኙ ክፍተቶችን ለማረም እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም