ቀጥታ፡

ኢትዮጵያውያን ለዓለም የገባነውን ቃል እውን ለማድረግ እስከ 11ኛው ሰዓት ችግኝ እንትከል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2016 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያውያን ዛሬ በአንድ ቀን ብሔራዊ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ለዓለም የገቡት ቃል እውን እስከሚሆን ድረስ ችግኝ መትከላቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቅርበዋል።

"ቃል ስንገባ የተናገርነውን የምንተገብር፣ ለቃል ትልቅ ክብር ያለን፣ የቃልን ክብደት የምንገነዘብ ስለሆንን፤ 600 ሚሊዮን አጋምሰን የመዳከም ምልክት እንዳይታይብን በርተተን እንስራ" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

"የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ እየተካሄ ባለው በሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር፤ መላው ህዝብ በከፍተኛ ደረጃ መሳተፉንና የእስካሁኑ ውጤት አበረታች እና አመርቂ መሆኑን በመጠቀስ ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም