ቀጥታ፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2016(ኢዜአ)፦የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 መካኒሳ ጌዶ ዋሻ በተደረገው መርሃ ግብር የስፖርት፣ ባህልና ኪነ ጥበብ ማህበራት ተሳትፈዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ዛሬ ችግኝን ተክሎ መመለስ ብቻ ሳይሆን በተፈለገው መጠን እንዲፀድቅ አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ከአረንጓዴ አሻራ ልማት ልታገኝ የሚገባትን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥቅም በተገቢው ሁኔታ እንድታገኝ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።


 

ለመርሃ ግብሩ ስኬታማነት ከቦታ መረጣና ዝግጅት አንስቶ አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

በአረንጓዴ አሻራ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ- ግብር ከማለዳ አንስቶ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተካሄደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ጀምበር የ600 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ላይ ሕብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ አስቀድመው ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም