በቤልጂየም ብራስልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተካሔደ - ኢዜአ አማርኛ
በቤልጂየም ብራስልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተካሔደ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2016(ኢዜአ)፦በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ-ግብርን በማስመለክት በቤልጂየም ብራስልስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ የችግኝ ተከላ ተከናውኗል።
“የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ በሚገኘው የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ያስተላለፉትን ጥሪ ተከትሎ በመላው ኢትዮጵያ የችግኝ ተከላ እየተካሄደ ይገኛል።
መርሃ-ግብሩን በማስመልከትም በብራስልስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪዎች እና ሠራተኞችም በኤምባሲው ቅጥር ግቢው ውስጥ የችግኝ ተከላ ማከናወናቸውን ከኤምባሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።