አረንጓዴ አሻራ ለአገር ልማት በትብብርና አብሮነት መቆምን በተግባር እያሳየ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አረንጓዴ አሻራ ለአገር ልማት በትብብርና አብሮነት መቆምን በተግባር እያሳየ ነው
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከችግኝ መትከልም ባለፈ ለአገር ልማት በትብብርና አብሮነት መቆምን በተግባር እያሳየ እንደሚገኝ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ ገለጹ።
በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኝ የመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር በመላ አገሪቱ እየተካሄደ ይገኛል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አመራርና ሰራተኞችም በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በመገኘት አሻራቸውን አኑረዋል።
የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ፤ አረንጓዴ አሻራ ከተጀመረ ስድስት አመት ያስቆጠረና በቴክኖሎጂ ተደግፎ ሲከናወን የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑን ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከችግኝ ተከላም ባለፈ ለአገር ልማት በትብብርና አብሮነት መቆምን በተግባር እያሳየ ያለ ብሔራዊ እቅድ መሆኑን አመልክተዋል።
የአስተዳደሩ አመራርና ሰራተኞች ከፀጥታ ተቋማት ጋራ በመሆን አሻራቸውን ማኖራቸውን ጠቅሰው ለአገር ልማትና እድገት ትብብራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የደን መመናመንን ከማስቀረት ባለፈ ለትውልድ የሚተርፍ አሻራ መሆኑንም ነው ዋና ዳይሬክተሯ የተናገሩት።
በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያዊያን ከማለዳው ጀምሮ አሻራቸውን ማኖራቸውን ቀጥለዋል።
በዚህም መሰረት በሁሉም የአገሪቷ አካባቢዎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ከልጅ እስከ አዋቂ ዜጎች ወጥተው ችግኞችን በመትከል ላይ ናቸው።