የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመራርና አባላት በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አሻራቸውን አኖሩ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመራርና አባላት በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አሻራቸውን አኖሩ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመራርና አባላት በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አሻራቸውን አኑረዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ተቋሙ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት መስዋዕትነት በመክፈል የኢትዮጵያን ሰላምና ደህንነት እያስከበረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ከተሰጠው ተልዕኮ ባሻገር በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ ተሳትፎ በማድረግ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች በርካታ ችግኞች መትከሉን ተናግረዋል።
ፖሊስ ከሕዝብ የወጣ የሕዝብ ልጅ በመሆኑ ከሕብረተሰቡ ጎን በመሆን በልማት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በማሳደግ የአገሪቷን ልማት አጠናክረን እናስቀጥላለን ሲሉ ኮሚሽነር ጀነራሉ መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።