በወረባቦ ወረዳ የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል - ኢዜአ አማርኛ
በወረባቦ ወረዳ የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል

ወረባቦ ፤ ነሐሴ 17/2016(ኢዜአ) ፡- በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ከፍተኛው የአመራር አባላት የተሳተፉበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአንድ መንፈስ በመላው ኢትዮጵያ ዓሻራችንን እናኑር ፤ አንድ ከሆንን ከዚህም በላይ እንችላለን ሲሉ ጥሪ ማስተላለፋቸው ይታወቃል፡፡
በዚህም አዋቂዎች ከ20 በላይ፣ ታዳጊዎች ከ10 በላይ በመትከል ለሀገር ያለንን ፍቅር፣ ለትውልድ ያለንን ስጦታ በተገቢው ስፍራ እንግለጥ በማለትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በአማራ ክልል ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተመረጡ የመትከያ ቦታዎች የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እየተከናወነ ሲሆን፤ ከነዚህም በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ አንዱ ነው።
በወረባቦ ወረዳ እየተካሄደ ባለው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን(ዶ/ር) እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።
በተጨማሪም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የህዝብ ግንኙነት አማካሪ ዶክተር ዘሪሁን ፍቅሩ፣ የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ቃልኪዳን ሽፈራው፣ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን እና ሌሎችም በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።