የአረንጓዴ አሻራችንን በማኖር ለሰው ልጆች ሁሉ የሚጠቅም መልካም ስራ እንስራ - ሼህ ሃጅ ኢብራሂም ቱፋ - ኢዜአ አማርኛ
የአረንጓዴ አሻራችንን በማኖር ለሰው ልጆች ሁሉ የሚጠቅም መልካም ስራ እንስራ - ሼህ ሃጅ ኢብራሂም ቱፋ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2016(ኢዜአ)፦ሁላችንም የአረንጓዴ አሻራችንን በማኖር ለሰው ልጆች ሁሉ የሚጠቅም መልካም ስራ እንስራ ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሃጅ ኢብራሂም ቱፋ ተናገሩ።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሼህ ሃጅ ኢብራሂም ቱፋ፤ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጫካ ፕሮጀክት አካባቢ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
የችግኝ ተከላና አካባቢን የማሳመር ጉዳይ የሰው ልጆች ሁሉ ኃላፊነት መሆኑን ሁላችንም የአረንጓዴ አሻራችንን በማኖር ለሰው ልጆች ሁሉ የሚጠቅም መልካም ስራ እንስራ ሲሉ ገልጸዋል።
በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከማለዳው ጀምሮ ከልጅ አስከ አዋቂ በሁሉም አካባቢዎች ዜጎች አሻራቸውን እያኖሩ ነው።
ከማለዳ የጀመረው መርሃ ግብር እስከ ምሽት የሚቀጥል ሲሆን አዋቂዎች ከ20 በላይ፤ ታዳጊዎች ደግሞ ከ10 በላይ ችግኞችን እንደሚተክሉ ይጠበቃል።
እየተደረገ ባለው ርብርብ መሰረት በመላ አገሪቷ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተያዘው እቅድ በስኬት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።