በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስከ አሁን 157 ሚሊዮን ችግኝ ተተክሏል- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት - ኢዜአ አማርኛ
በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስከ አሁን 157 ሚሊዮን ችግኝ ተተክሏል- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2016(ኢዜአ)፦በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ- ግብር እስካሁን 157 ሚሊዮን ችግኝ መተከሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
በአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተካሄደ ይገኛል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ መርሐግብሩን በማስመልክት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 157 ሚሊዮን ችግኝ መተከሉን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ የሚገኘው የሁኔታዎች መከታተያና የመረጃ ማደራጃ ማዕከል የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላን አስመልክቶ ያሉ መረጃዎችን እንደሚያደርስም ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር የ600 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ሕብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።