በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2016(ኢዜአ)፦በቻይና ቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
በኤምባሲው ቅጥር ግቢ በተደረገው መርሃ- ግብር በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው አሻራቸውን አስቀምጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አሻራችንን እናኑር በማለት ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል።