የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2016(ኢዜአ)፦የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ጎጀብ ከተማ አካባቢ አረንጓንዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር የ600 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ሕብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።