ቀጥታ፡

በኮትዲቭዋር አቢጃን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ተከናወነ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2016(ኢዜአ)፦በኮትዲቭዋር አቢጃን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አመራሮችና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

በኮትዲቭዋር የኢትዮጵያ አምባሳደር ሽታዬ ምናለና የሚሲዮኑ ሰራተኞች በመርሃ-ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል።


 

መርሃ-ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር በሚል ያቀረቡትን አገር አቀፍ ጥሪን ተከትሎ የተከናወነ መሆኑን ኤምባሲው አመልክቷል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም