በሴቶችና በማህበረሰብ የተጠበቁ የተፈጥሮ ደኖች ለአረንጓዴ አሻራችን

በሚስባህ አወል (ኢዜአ)

ሴት አርሶ አደር ሜሪ ኦፍሬ በናይጀሪያ ኦሎን መንደር ነዋሪ ስትሆን፤ የአምስት ልጆች እናት ነች። ባለቤቷን ሞት ነጥቋት ልጆቿን የምታሳድገው ብቻዋን ነው። በመንደሯ አፊ ተብሎ የሚጠራ ጥብቅ ደን አለ። ሜሪ ኦፍሬ ኑሮዋን የምትመራው በዚህ ጥብቅ ደን አቅራቢያ ባላት አነስተኛ የእርሻ ማሳን ከዚሁ ጥብቅ ደን በምታገኘው ትሩፋት እንደሆነ ነው ለአልጄዚራ የገለጸችው።

ጠንካራዋ ሜሪ አፍሬ ከመንደሯ ሴቶች ጋር በመተባበር የአካባቢቸውን ስነ ምህዳር ለመጠበቅ በማህበር ከተደራጁ  አባሎቿ ጋር በመሆን በዓለም አማቀፍ ደረጀ  የሚታወቀውን ይሄንኑ በአቅራቢያቸው የሚገኘውን ኦፊን ጥብቅ ደን ከህገ-ወጥ ጨፍጫፊዎች  መጠበቅ ከጀመሩም ሰነባብተዋል።

በናይጄሪያ ክሮስ ሪቨር ግዛት የሚገኘው ይኸው ታዋቂ የኦፊን ደን በህገወጥ መንገድ ለማገዶ እንጨትና ለሌሎች አገልግሎት የሚውሉ ዛፎችን በሚቆርጡ ደን በሚመነጥ  ህገ-ወጥ  አካላት ሳቢያ የመጥፋት አደጋ ከተጋረጠባቸው የደን ሀብቶች መካከል አንዱ ሆኖ ነበር።የአፊን ጥብቅ የደን ሀብት በናይጄሪያ ብቻ ሳይሆን፤በዓለም ላይ ከፍተኛ የደን ጭፍጨፋ እንሚካሄድባቸውና  በተደጋጋሚ ስማቸው ከሚጠራ አካባቢዎች  ግንባር ቀደም ተጠቃሽ እንደሆነም መረጃዎች ያመለክታሉ።

የአፊ ጥብቅ ደንም ሆነ በውስጡ የተጠለሉ የዱር እንሰሳትና የሚገኙ ብዝሃ ህይወቶች ዝርያቸው ተመናምኖ ለመጥፋት ተቃርቦ እንደነበር  አልጀዚራ የሰራው ዘጋቢ ፊልም ያመለክታል።
ሜሪ አፍሬን ጨምሮ በአካባቢዋ በማህበር የተደራጁ ሴቶች የአፊን ጥብቅ የደን ሀብት ከህገ-ወጥ ጨፍጫፊዎች ከመጠበቅ ባለፈ ስነየአካባቢውን ስነምህዳ ልምላሜውን ጠብቆ አረንጓዴ እንደለበሰ  የዛረውን ትውልድ እየጠቀመ ለተተኪው ትውልድ እንዲሸጋገር ችግኞችን በመትከልና ተንከባክቦ በዘላቂነት ለማልማት ቁልፍ ሚና እንዳላቸውና ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ  አልጀዚራ በዘጋቢ ፊልም ጠቅሷል።

በዘጋቢ ፊልሙ እንደሚያመለክተው ሜቤሪ አንፍሬና ባልደረቦቿ ጥብቅ የደን ሀብቱን ለመጨፍጨው ወደ አካባቢያቸው የሚመጡ ህገ-ወጥ የደን ጨፍጫፊዎችን በመከታተልና ለአካባቢው የጥበቃ አካላት በማጋለጥ የአፊን ጥብቅ ደን ለመታደግ  ያላቸው ሚና የላቀ ነው።
ሜሪና አንፍሬ እና ባልደረቦቿ የኦፊ ጥብቅ የደን ሀብት ተራራው፣ጋራ ኮረብታውን፣ ሜዳ ሸንተረሩን፣ በጥቅሉ  የአካባቢውን  የስነ ምህዳር በአግባቡ ጠብቆ፣ አልምቶና ተንከባክቦ  በማቆየት የሚያገኙት ትሩፋት  ምን ያህል የሕይወት መድን እንደሆናቸው ጠንቅቀው የተረዱ ናቸው። በመሆኑም አንዳቸው ለአንዳቸው የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች የሕልውናቸው መሰረት መድን እንደሆኑም ነው የሚገልጹት።

ከአንፊ ጥብቅ ደን ለምግብነትና ለባህላዊ መደኃነትነት የሚውሉ የተለያዩ የፍራፍሬዎች እንደሚያገኙ  ሜሪ አፍሬ ትገልጻለች። እነዚን የአፊን ጥብቅ ደን ገፀ-በረከቶች ምግብነትም ባህላዊ መድኃኒት እየተጠቀሙበት በመሆኑ የመጠበቁን፣ የማልማቱንና የመንከባከቡን ተግባር የሚከውኑት በፍላጎትና በደስታ ነውም ትላለች። በተለይ ለእሷ ይህን ዘርፈ  ብዙ ፋይዳ ያለውንና ልጆቿን የምታሳድግበትን የአንፊ ጥበቅ ደንን  ከህገ-ወጥ ጨፍጫፊዎች ጠብቆ መከላከል፣ ማልማትና መንከባከብ ደስታዋም መዝናኛዋም ጭምር እንደሆነ ትገልጻለች።

በማህበር የተደራጁት ሴቶች የአንፊ ጥብቅ ደንን ከህገ-ወጥ ጨፍጫፊዎች ለመጠበቅ፣ ችግኞችን በመትከል ለማልማትና ለመንከባከብ  የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በየጊዜው ተገናኝተው እንደሚመካከሩም ነው አልጀዚራ በዘጋቢ ፊልሙ ያመላከተው።

በአገራችን ኢትዮጵያ በሴቶች ብቻ ያሳተፈ ሳይሆን በመላ ማህበረሰብ ተሳትፎ የተጠበቀ የተፈጥሮ የደን ሀብት በዚህ በመገባደድ ላይ በሚገኘው  ዓመት መጀመሪያ አካባቢ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሣይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) መመዝገቡን ስንቶቻችን እናስታውሳል አልያም እናውቃለን?

የጌዴኦ ህዝብ በጥምር ግብርና ሥራዎች የዕጽዋዕት፣ የፍራፍሬ፣ የሰብል ምርቶችና በጣዕሙ የሚታወቀውን የይርጋጨፌ ቡና በማምረት ይታወቃል።ህብረተሰቡ ሀገር በቀል ዕውቀት ተጠቅሞ የአካባቢው የአየር ፀባይና የተፈጥሮ ሚዛን የተስተካከለና ለህይወት ተስማሚ እንዲሆን፣የመሬት አጠባበቅ፣ አጠቃቀም፣ አያያዝና አስተዳደር ልምዱ በዩኔስኮ እንዲመዘገብም አስችሎታል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ቀልብን ከሚስቡ የቱሪዝም ኃብቶች መካከል የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር በእጅጉ አስደማሚ ነው። ለዚህ መነሻው በተለያዩ ረጅም ዕድሜን ባስቆጠሩ  ጥቅጥቅ ባሉ ግዙፍ ሀገር በቀል ዛፎችና ደንና ጫካ  ተፈጥሮ አስጊጣ ያስዋበች መሆኑ ነው።ጌዴኦ ደን ብቻ ሳይሆን ጥምር የግብርና ልማት የሚካሄድበትም ነው። ቡናው ከዋርካው ፡ ከዋንዛው ጋርና መሰል ሀገር በቀል ዛፎች ጋር ተሰናስሎ አብሮ በጥምር የሚለማበት ነው፡፡

የይርጋ ጨፌ ቡና የሀገር በቀል ዛፎችና የተለያዩ ፍራፍሬዎች ተክሎች  ተሰናስለውና መስተጋብር ፈጥረው ጥላ ከለላ በመሆናቸው ተፈጥሯዊ ጣዕሙን ይዞ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳጅና ተወዳዳሪ የሆነው ። ጌዴኦ በትውልድ ቅብብሎሽ ተጠብቆ የዘለቀው ይኸው የተፈጥሮ ደን ዛሬ ላይ በመላ ሀገሪቱ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ሀገራችን በየዓመቱ በሕዝብ ንቅናቄ እየተተገበረ በሚገኘው የአረንጋዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብርን ተግባራዊ እያደረገች ትገኛለች።ይህም በጌዴኦ አካባቢ የሚታየው የቆየ ጥብቅ ደን አያያዝና የጥምር ግብርና ልምታ በመላ ሀገራችን ተዳርሶ ባህል እንዲሆን ያስችላል።

አገራችን ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አሕመድ አነሳሺነት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት አቤይት ምዕራፎች በየዓመቱ የክረምት ወቅት እተገበረችው የሚገኘው የአረንጋዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የደን ሽፋንን ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ በሀገራችን የበርካታ አእዋፋት፣ እንስሳትና አዝርዕት መገኛ እነቶን ጭምር ይዛ እንድትቀጥል  የሚያስችል ጭምር ነው። ይህም ሰው ከተፈጥሮ ጋር እንዴት ሰናስሎ፣ ተጋምዶና ተዛምዶ መኖር እንደሚችል የሚያሳይ ነው።

በዘንድሮው የአረንጋዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የታቀደ ሲሆን ከዚህ ውስጥ  ዓርብ ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአንድ ጀንበር  600 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ሀገራችን ቀን ቆርጣና ዝግጅቷን  አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ “አረንጓዴ አሻራ” ብላ የሰየመችው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ማካሄድ ከጀመረች ዘንድሮ 6ኛ ዓመት ላይ ደርሳለች። ከ2011 ዓ.ም እስከ 2014 ዓ.ም ባካሄደችው የመጀመሪያ ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 20 ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል አቅዳ 25 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ከዕቅድ በላይ ማሳካቷን ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በ2015 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል። ባለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት በተካሄዱት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮች ከ32 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግችግኞች መተከላቸውን የሚኒስትሩ መረጃ ያሳያል። 

የጌዴኦ ህዝብ በጥምር ግብርና ልማት ልምድን በመቀመር በሴቶችና በማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ተሳትፎ የተጠበቁ የተፈጥሮ የደኖ አብቶችን ተንከባክቦና ጠብቆ በማቆየት በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮች በነቂስ ወጥተን በመሳተፍ አገራችንን አረንጓዴ ለማልበስ እያደረግነውን ያለውን ብርቱ ጥረትና ትጋት አጠናክረን በመቀጠል ሁላችንም የተሻለች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እናውርስ።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም