የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመቶችን ሲሰጥ ሽግሽግ በማድረግ ከኃላፊነትም አንስቷል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 16/2016(ኢዜአ):-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመቶችን ሲሰጥ ሽግሽግ በማድረግ ከኃላፊነትም ማንሳቱን አስታወቀ::

የከተማ አስተዳደሩ በ2016 ዓ. ም. ባደረገው የስራ አፈፃፀም ግምገማ የተገኙ ውጤታማ ጥንካሬዎችን በማላቅ የተለዩ ድክመቶችን በማረም ላይ ይገኛል::

የተጀመረውን የተቋማት ግንባታና የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥቷል ፣ ሽግሽግ አድርጓል እንዲሁም የተወሰኑትን ከኃላፊነት አንስቷል::

በዚህም መሰረት:-

1. አቶ አብርሃም ታደሰ - የከንቲባ የአደረጃጀት አማካሪ

2.. አቶ ይመር ከበደ- የመንግስት ልማት ድርጅቶች ባለስልጣን ሃላፊ

በከተማ ማዕከል ደረጃ የተሰጡ ሹመቶች:-

1. አቶ አደም ኑሪ - የፕላንና ልማት ቢሮ ሃላፊ

2. አቶ ቢኒያም ምክሩ - የገቢዎቸ ቢሮ ሃላፊ

3. ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ- የንግድ ቢሮ ሃላፊ

4. ዶ/ር ዳዲ ወዳጆ - የከንቲባ ስትራቴጂክ ጉዳዮች አማካሪ

5. አቶ ተስፋዬ ደንድር - የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ሃላፊ

6. አቶ ማቆያ አለማየሁ - የግንባታና ዲዛይን ምክትል ቢሮ ሃላፊ

7. አቶ አስመሮም ብርሃኔ - የትራንስፖርት ምክትል ቢሮ ሃላፊ

8. አቶ ተስፋዬ ጫኔ - የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ሃላፊ

9. አቶ ዩኑስ አደም - የመሬት ልማትና አስተዳደር ምክትል ቢሮ ሃላፊ

10. አቶ አዳነ ሱሌ - የገቢዎች ቢሮ ፅ/ ቤት ሃላፊ

11. ወ/ሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ - የገቢዎች ምክትል ቢሮ ሃላፊ

12. አቶ ዘገየ በላይነህ - የፀረ-ሙሰና ኮሚሽን ምክትል ሃላፊ

13. ወ/ሮ ፀሀይ ኪባሞ - የበጎ ፈቃድና ህዝብ ተሳትፎ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር

14. ኮ/ር አህመድ ሙሃመድ - የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ሃላፊ

15. ⁠አቶ ከፍያለው ታደሰ- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ሃላፊ

16. ⁠አቶ ዘመኑ ታደሰ - የመብራት አገልግሎት ፅ/ ቤት ሃላፊ

17. ⁠ወ/ሮ ወይንሸት ብዛኔ - የከንቲባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ምክትል ሃላፊ

18. ⁠አቶ አሰፋ ቶላ - የዲዛይንና ግንባታ ማማከር ፅ/ቤት ሃላፊ

በክፍለ ከተማ ደረጃ

1. ወ/ ሮ ካባ መብራቱ - የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ

2. ⁠ወ/ሮ አበባ እሸቴ - የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ

3. ⁠አቶ ጌታሁን አበራ - የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ

4. ⁠አቶ መብራቱ ደሴ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ፓርቲ ፅ/ ቤት ሃላፊ በመሆን ተሹመዋል::

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም