ቀጥታ፡

አሸንድዬ፣ ሻደይ፣ አሸንዳ፣ ሶለል ሰሜን ኢትዮጵያን የሚያደምቃት ድንቅ የነሀሴ ወር ገፀ በረከቷ ነው -አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 16/2016 (ኢዜአ)፦ አሸንድዬ፣ ሻደይ፣ አሸንዳ፣ ሶለል ሰሜን ኢትዮጵያን ይበልጥ የሚያደምቃት ድንቅ የነሀሴ ወር ገፀ በረከቷ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሸንድዬ፣ ሻደይ፣ አሸንዳ፣ ሶለል፣ የልጃገረዶች የደስታ ቀን ነው ብለዋል፡፡

ይህ በዓል በሀገራችን የሰሜኑ ክፍል በዋናነት በአማራ እና ትግራይ ክልሎች በልጃገረዶች ጭፈራ እና ዝማሬ በድምቀት ይከበራል ብለዋል።

አሸንድዬ፣ ሻደይ፣ አሸንዳ፣ ሶለል ሰሜን ኢትዮጵያን ይበልጥ የሚያደምቃት ድንቅ የነሐሴ ወር ገፀ በረከቷ መሆኑን በመግለጽም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም