ለሀገራችን የዕድገት ጉዞ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራ ወሳኝ ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
ለሀገራችን የዕድገት ጉዞ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራ ወሳኝ ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ ፤ነሐሴ ፤16 /2016 (ኢዜአ)፦ለሀገራችን የዕድገት ጉዞ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራ ወሳኝ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
የብሔራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ሶስተኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንደገለጹት፤ በስብሰባው የምክር ቤቱን አጠቃላይ የስራ ክንውን፣ የ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ትግበራ አፈጻጸምን ገምግመናል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የIT ፓርክን በተመለከተ በተሰጡ ስራዎች ላይ የክንውን ሪፖርትን የገመገምን ሲሆን የብሄራዊ ዲጂታል የመንግስት ስትራቴጂ ቀርቦ በምክር ቤቱ አባላት ውይይት ተደርጎበታል ነው ያሉት፡፡