ቀጥታ፡

በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አመራሮችና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 16/2016(ኢዜአ)፦በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አመራሮችና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

በኤምባሲው ቅጥር ግቢ በተካሄደው መርሐ ግብር ላይ የኤምባሲው ምክትል ሚሲዮን መሪ ሮባ ዳሜ፣የኤምባሲው ዲፕሎማቶችና አጠቃላይ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ኤምባሲው በየዓመቱ ተሳትፎ እያደረገ እንደሚገኝ አመልክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር በማለት መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም