ቀጥታ፡

በ17ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ ሽኝት ይደረግለታል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 16/2016(ኢዜአ)፦በፓሪስ በሚደረገው 17ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ አሸኛኘት እንደሚደረግለት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ከነሐሴ 22 እስከ ጳጉሜን 3 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳሉ።

በውድድሩ ላይ ከ184 አገራት የተወጣጡ 4 ሺህ 400 አትሌቶች በ22 የስፖርት ዓይነቶች ይወዳደራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያም በአትሌቲክስ ስፖርት ስድስት ተወዳዳሪዎችን ታሳትፋለች።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በውድድሩ ላይ የሚሳተፈውን የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ልዑካን ቡድን አበረታተዋል።

መንግስት ለልዑኩ አስፈላጊውን ድጋፍና ማበረታቻ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ ከሰዓት በኋላ አሸኛኘት እንደሚደረግለት ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ ከሶስት ዓመት በፊት በቶኪዮ በተካሄደው 16ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች በ1 የወርቅ ሜዳሊያ 59ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም