ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በድሬዳዋ ስታዲየም ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 15/2016(ኢዜአ)፦ የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በድሬዳዋ ስታዲየም እንደሚጀመር የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ።

የፕሪሚየር ሊጉ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ዛሬ በማህበሩ ዋና ጽህፈት ቤት ተካሄዷል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ክፍሌ ሰይፈና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ ባህሩ ጥላሁን ተገኝተዋል።

የውድድር ዓመቱ መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም በድሬዳዋ ስታዲየም እንደሚጀመር አክሲዮን ማህበሩ ገልጿል።

በፕሪሚየር ሊጉ 19 ክለቦች እንደሚሳተፉም ተመላክቷል።

አርባ ምንጭና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደጉ ክለቦች ናቸው።

መቀሌ ሰባ እንደርታ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲና ስሑል ሽሬ ዳግም ወደ ውድድር መመለሳቸው ይታወቃል።

በ2017 ዓ.ም የውድድር ዘመን በ19 ክለቦች መካከል ውድድር ተደርጎ 5 ክለቦች ወደ ከፍተኛ ሊግ እንደሚወርዱ ተገልጿል።

በ2018 የውድድር ዓመት ሁለት ክለቦች ደግሞ ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንደሚያድጉም እንዲሁ።

ይህንንም ተከትሎ በ2018 ዓ.ም ሊጉ ወደነበረበት 16 ክለቦች እንደሚመለስ ነው ማኅበሩ ያስታወቀው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም