ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና ዥያንግ ፖሊስ ኮሌጅ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 15/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና ዥያንግ ፖሊስ ኮሌጅ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ በሰንዳፋ ተፈራርሟል። 

ስምምነቱ ሁለቱ የትምህርት ተቋማት ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር፣ፖሊሳዊ ስነ ምግባርን ይበልጥ ለማሳደግ የሚያግዙ ሞጁሎችን በጋራ ማዘጋጀት እንዲሁም የተለያዩ ስልጠናዎችንና የትምህርት እድሎችን ማመቻቸት ያስችላቸዋል።

ተቋማቱ በስምምነቱ አማካኝነት የትራፊክ አደጋን ሊቀንሱ የሚችሉ የወንጀል መከላከልና የምርመራ ስራዎችን ለማከናወንና በቴክኖሎጂ ሽግግር በትብብር እንደሚሰሩ ተጠቁሟል።


 

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ ኢትዮጵያና ቻይና ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ትብብር እንዳላቸው ገልጸው ዩኒቨርሲቲውም ይህንኑ ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን ለማጎልበት እንደሚሰራ አመልክተዋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ለመጡ የቻይና ዥያንግ ፖሊስ ኮሌጅ የልዑካን ቡድን ምስጋና ማቅረባቸውን ከኢትዮጵያ ፌዴሬራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም