የአሜሪካዊው ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የሙስና ወንጀል ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል

ሴናተሩ ሰርተውታል በተባሉበትና በተከሰሱበት ወንጀል በደረሰባቸው ጫና ምክንያት ከሃላፊነታቸው ለመልቀቅ ማመልከቻቸውን ለኒው ጄርሲው አገረ ገዥ ፊል መርፊ ማስገባታቸውን የዛሬው የሲቢኤስ ኒውስ ዘገባ ያሳያል።

ይሄንን ተከትሎም በአሜሪካ በመጪው ህዳር ላይ በሚደረገው ምርጫ እንደማይሳተፉም በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ሴናተር ቦብ ሚኔንዴዝ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ በኒውጄርሲ በንግድ ስራ ላይ ከተሰማሩ 3 የግብጽ ሰዎች እጅ ወርቅ እና ጥሬ ገንዘብ ጉቦ መቀባላቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ይህም ሴናተሩ ራሳቸውን ለግብጽ መንግሥት ወኪል አድርገው በመቆም ሰርተዋል የሚል ክስ ሲቀርብባቸው እንደነበረ ይታወቃል።

በዚህም በዘረፋ፣ ጉቦ በመቀበል፣ ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም፣ በሴራ፣ ፍትህን በማደናቀፍና መሰል 16 ወንጀሎች ላይ ተሳትፎ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በመሆኑም በሚቀጥለው ህዳር ወር በሚካሄደው ምርጫ ዴሞክራቶችን ወክለው የሚወዳደሩት ቦብ ሜኒዴዝ ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንዲለቁ መሆናቸውን ተከትሎም በሌላ እጩ እንደሚተኩ ተገልጿል።

የ70 ዓመት አዛውንቱ ሴናተር ቦብ ሚኒንዴዝ ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ከሀገሪቱ ወታደራዊ እርዳታ ማመቻቸታቸውም ከተከሰሱባቸው ጉዳዮች አንዱ ሆኖ ቀርቧል።

አጋሮቻቸውን ከወንጀል በመከላከል፣ አለአግባብ እንዲበለጽጉ በባለቤታቸው በኩል ከግብጽ የደህንነት ሰዎች ጋር ግኑኝነት በመፍጠር ስልጣንን አላግባብ ተጠቅመዋል ሲል አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል።

የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር ሆነው ስራቸውን እየሰሩ ስለመሆናቸው የሚናገሩት ቦብ ሚኔንዴዝ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሳምንታት ያክል ምርመራ ሲደረግባቸው እንደቆየ ቢገለጽም እሳቸው አሁንም አልፈጸምኩም እያሉ ይገኛሉ።

ሴናተሩ “እኔ በህዝብ ፊት የገባሁትን ቃል አልጣስኩም፣ ከሀገር ወዳድነቴና አርበኝነቴ ውጭ ምንም አልሆንኩም ለማንም ሀገር የምሰራው ጉዳይ የለኝም” ማለታቸውም ተገልጿል።

እኚህ አዛውንት ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ በተጠረጠሩበት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙና ከተፈረደባቸው ቀሪ ዘመናቸውን በማረሚያ ቤት ሊያሳልፉ እንደሚችሉም አሶሲዬትድ ፕሬስን ጨምሮ የተለያዩ የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡት ይገኛሉ።

May be an image of 1 person

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም