ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ከየመን ጋር ያላትን ለረጅም ጊዜያት የዘለቀ ታሪካዊ ግንኙነት ለማሳደግ ትሰራለች

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና የመን ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጎልበት በጋራ እንደሚሰሩ አስታወቁ።

በኳታር፣ ኢራንና የመን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፈይሰል የሹመት ደብዳቤያቸውን ለየመን ፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ዶክተር ራሽድ ሙሐመድ አል-አሊሚ ዛሬ በኤደን ከተማ አቅርበዋል።

አምባሳደር ፈይሰልና ዶክተር ራሽድ በውይይታቸው ኢትዮጵያና የመን ለረጅም ጊዜያት የዘለቀ ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳላቸው አንስተዋል።

የአገራቱን የቆየ ወዳጅነት በፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ሌሎች መስኮች ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግና በጋራ ለመስራት ከመግባባት ላይ መድረሳቸውን ኢዜአ ዶሃ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም