ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ለኢትዮጵያን ገጽታ ግንባታ የበኩላቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል - አምባሳደር ደሴ ዳልኬ

አዲስ አበበ፤ነሐሴ 13/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ተማሪዎች የኢትዮጵያን ገጽታ ለመገንባት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ በኮሪያ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሴ ዳልኬ ገለጹ።

አምባሳደር ደሴ በኮሪያ ሪፓብሊክ ዋና ከተማ ሴኡል በተደረገው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል።

በኮሪያ ሪፐብሊክ በሚማሩ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች መካከል ትብብር ለመፍጠር ውይይቱ ወሳኝ ሚና እንዳለው አምባሳደሩ ገልጸዋል።

ኤምባሲው ለተማሪዎች በሁሉም አካባቢዎች የሚቻለውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አመልክተዋል።

ተማሪዎቹ ያገኙትን እውቀትና ልምድ ተጠቅመው የአገራቸውን ልማት እንዲደግፉ ጠይቀዋል።

ለኢትዮጵያ ጥብቅና ለመቆምና የአገራቸውን ገጽታ ለመገንባት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሚገባቸው አምባሳደሩ ማሳሰባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም