ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት የፊታችን ረቡዕ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፤ነሐሴ 13 /2016 (ኢዜአ)፦ የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ረቡዕ ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ።

በሊጉ 19 ክለቦች ይሳተፋሉ።

አርባ ምንጭና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደጉ ክለቦች ናቸው።

መቀሌ ሰባ እንደርታ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲና ስሑል ሽሬ ዳግም ወደ ውድድር መመለሳቸው ይታወቃል።

በ2017 ዓ.ም የውድድር ዘመን በ19 ክለቦች መካከል ውድድር ተደርጎ 5 ክለቦች ወደ ከፍተኛ ሊግ እንደሚወርዱ ተገልጿል።

በ2018 የውድድር ዓመት ሁለት ክለቦች ደግሞ ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንደሚያድጉም እንዲሁ።

ይህንንም ተከትሎ በ2018 ዓ.ም ሊጉ ወደነበረበት 16 ክለቦች እንደሚመለስ ነው ማኅበሩ ያስታወቀው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም