ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ቡና በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከኬንያ ፖሊስ ጋር አድርጎ ያለግብ ተለያየ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 12/ 2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ቡና በ2024/25 የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከኬንያው ኬንያ ፖሊስ ጋር አድርጎ 0 ለ 0 ተለያይቷል።

የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በናይሮቢ ንያዮ ብሔራዊ ስታዲየም ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ ተካሂዷል።

ኢትዮጵያ ቡና ለጨዋታው 18 ተጫዋቾችና 6 የአሰልጣኝ ቡድን አባላትን በመያዝ በትናንትናው እለት ነበር ናይሮቢ የገባው።

ቡናማዎቹ በገቡበት ዕለትም ጨዋታው በሚደረግበት ሜዳ ላይ ልምምዳቸውን አድርገው በዛሬው እለት ጨዋታቸውን አድርገዋል።

በዚህም ኢትዮጵያ ቡና በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታው ከኬንያው ኬንያ ፖሊስ ጋር አድርጎ 0 ለ 0 ተለያይቷል። 

የሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታ እሁድ ነሐሴ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚካሄድ መሆኑን የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል።

ቡናማዎቹ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፋ በሁለተኛው ዙር ከግብፁ ዛማሌክ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

ኢትዮጵያ ቡና በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ ነው።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም