የኢትዮጵያ አየር መንገድ መግለጫ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መግለጫ
እ.ኤ.አ. ኦገስት 16 ቀን 2024 ዓ.ም. ጠዋት ከህንድ ሙምባይ ወደ አዲስ አበባ ለመብረር በዝግጅት ላይ ወደነበረ አውሮፕላን የሚጫኑ ሻንጣዎችን ይዞ ወደ አውሮፕላኑ በመጎተት ላይ በነበረ ጋሪ ላይ ከተጫኑ ሻንጣዎች በአንዱ እሳት ታይቷል።
ክስተቱ ጋሪው ከራምፕ አካባቢ ወደ አውሮፕላኑ በመሄድ ላይ ሳለ እንደተከሰተ ተስተውሏል።
ይህንንም ክስተት የተመለከቱ በሙምባይ ያሉ የደህንነት ፣ የጸጥታ እና የእሳት አደጋ ባለሞያዎች እሳት የያዘውን ሻንጣ በመለየት እሳቱን በቁጥጥር ስር አውለዋል።
አውሮፕላኑ አስፈላጊው ተጨማሪ የደህንነት ፍተሻ ከተደረገለት በኋላ እና አስጊ ነገር አለመኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ በረራውን አካሂዷል።
የሙምባይ ኤርፖርት ባለስልጣናትና የሚመለከታቸው አካላት የክስተቱን ምንጭ በመመርመር ላይ በመሆናቸው ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን የምናሳውቅ ይሆናል።