የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 11/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።
በቢሾፍቱ በሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ባለው የምርቃት ስነ-ስርአት ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትርና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ፍጹም አሰፋ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች፣ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
ዩኒቨርሲቲው ዛሬ የሚያስመርቃቸው ተማሪዎች በምህንድስና፣ በጤና እና በሃብት አስተዳደር ዘርፍ ትምህርታቸውን በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም በምህንድስና የትምህርት ዘርፍ በዶክትሬት ዲግሪ የተከታተሉም ናቸው ተብሏል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የሰራዊቱን ስምና ዝና በሚመጥን መልኩ የተዋቀረ ሲሆን ከመማር ማስተማር ስራዎች በተጎዳኝ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ስራዎችን እና ሌሎች ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ ተግባራትን በመስራት ላይ ይገኛል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በሶስት ኮሌጆች እና በአንድ የምርምር እና ልማት ኢንስቲትዩት የተዋቀረ መሆኑም በዚሁ ወቅት ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በ2025 ከአፍሪካ አምስት ምርጥ ዩኒቨርስቲዎች አንዱ የመሆን ራዕይ ሰንቋል።
ዩኒቨርሲቲው ከኢትዮጵያ ተማሪዎች በተጨማሪ ከጎረቤት ሀገራት የመጡ ተማሪዎችንም አሰልጥኖ ያስመርቃል።