ቀጥታ፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከአሜሪካ የንግድ ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 10/2016(ኢዜአ)፦የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከአሜሪካ የንግድ ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጨምሮ በኢትዮጵያ የአሜሪካ የንግድ ምክር ቤት አባላት ተሳትፈዋል።


 

በዚሁ ጊዜ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ተግባራዊ ያደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ እና ስትራተጂክ ጉዳዮች ላይ ገለፃ አድርገዋል።

ውይይቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ የንግድ ምክር ቤት አባላት ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር መስተጋብር እንዲፈጥሩ ያስቻለ መሆኑም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም