ቀጥታ፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ከኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፈዴሬሽን ጋር በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 10/2016(ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ከኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፈዴሬሽን ጋር  በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ከኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፈዴሬሽን ጋር  በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

መርኃ ግብሩ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ኪዳነ ምህረት አካባቢ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

"የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ሀሳብ በመካሄድ ላይ በሚገኘው ስድስተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የተለያዩ ተቋማት አሻራቸውን እያሳረፉ ነው። 

በመርኃ ግብሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበበ ተቀባና የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ተገኝተዋል፡፡

በችግኝ ተከላው ላይ የተገኙት የክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የኮንፌዴሬሸኑ አካላት በመርኃ ግብሩ 10 ሺህ ችግኞች እንደሚተከሉ ተገልጿል ። 

በዘንድሮ  አረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር  7 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ግብ መጣሉ ይታወቃል ።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም