የሰቆጣ ቃል ኪዳን የመቀንጨርን ችግር ከሀገራችን ለማጥፋት በመንግስት ባለቤትነት የሚተገበር የሀገር በቀል መፍትሔ ውጤታማነት ማሳያ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
የሰቆጣ ቃል ኪዳን የመቀንጨርን ችግር ከሀገራችን ለማጥፋት በመንግስት ባለቤትነት የሚተገበር የሀገር በቀል መፍትሔ ውጤታማነት ማሳያ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 9/2016(ኢዜአ)፦የሰቆጣ ቃል ኪዳን የመቀንጨርን ችግር ከሀገራችን ለማጥፋት በመንግስት ባለቤትነት የሚተገበር የሀገር በቀል መፍትሔ ውጤታማነት ማሳያ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ዛሬ የኢትዮጵያ ምግብ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን፣ የምግብ እና ሥርዓተ ምግብ ስትራቴጂ እና የሰቆጣ ቃል ኪዳን እንዲሁም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን የ2016 ዓ.ም አፈፃፀም እንዲሁም የ2017 ዓ.ም ዕቅድን ገምግመናል ብለዋል፡፡
የዜጎችን የምግብ እና የሥርዓተ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የጤና መድን አገልግሎትን ለማሳደግ በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦችን ለማገዝ የመንግሥት ፣ የመላው ህዝባችን እና የአጋር አካላት ሀብቶችን በጋራ ማሰባሰብና በውጤታማነት አሟጦ መጠቀም ያስፈልጋል ሲሉም ገልጸዋል።
በተጨማሪም ከሌሎች ሀገር በቀል ንቀናቄዎች እና ትግበራዎች ጋር አስተሣሥሮ መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በጋራ አቅጣጫ አስቀምጠናል ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡