ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን የሚያደርግበት ቦታና ቀን ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 9/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን በሞሮኮ አስተናጋጅነት በሚካሄደው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ሁለት የማጣሪያ ጨዋታዎቹን የሚያካሒድበት ቦታና ቀን ይፋ ሆኗል።

በማጣሪያው ኢትዮጵያ በምድብ 8 ከጊኒ፣ታንዛንያና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር መደልደሏ ይታወቃል።

ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከታንዛንያ ጋር ነሐሴ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ዳሬ ሰላም ላይ እንደሚያደርግ ኢዜአ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሁለተኛና የሜዳ ጨዋታውን ጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ዳሬ ሰላም በሚገኘው ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም (የታንዛንያ ብሔራዊ ስታዲየም) እንደሚያደርግ ገልጿል።

በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 48 አገራት በ12 ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በአፍሪካ ዋንጫው ደግሞ 24 አገራት ይሳተፋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም