በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል ሁለተኛው ዙር ውይይት ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል ሁለተኛው ዙር ውይይት ተደረገ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 7/2016(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል ሁለተኛው ዙር ውይይት መካሔዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹ።
አምባሳደር ታዬ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ሁለተኛው ዙር ውይይት በተርኪዬ አመቻችነት በአንካራ መካሄዱን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ህጋዊ ፍላጎትም በሰላማዊ መንገድ ከጎረቤቶቻችን ጋር በመተባበር እንደሚፈፀም እርግጠኛ ነኝ" ሲሉም አስፍረዋል።
የተርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ከውይይቱ በፊት ኢትዮጵያን በመጎብኘታቸውም ምስጋና አቅርበዋል።