ቀጥታ፡

ለ33ኛው የኦሊምፒክ ልዑካን በብሔራዊ ቤተመንግስት የእውቅና መርሃ-ግብር እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 7/2016(ኢዜአ)፦በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ለተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በብሔራዊ ቤተመንግስት የእውቅና መርሃ-ግብር እየተካሔደ ነው ።

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል የስራ ሃላፊዎች ፣ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የኦሎምፒክ ኮሚቴ እንዲሁም የውድድሩ ተሳታፊ አትሌቶች በመርሀ-ግብሩ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ በአትሌቲክስና ውሃ ዋና ስፖርት 38 ስፖርተኞችን አሳትፋለች። 1 የወርቅና 3 የብር አጠቃላይ 4 ሜዳሊያዎችን በማግኘት 47ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም