ቀጥታ፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲው በተሳካ ሁኔታ እንዲተገበር የፍትሕ እና የፀጥታ ተቋማት ሚና የላቀ ነው - አቶ አሕመድ ሽዴ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 7/2016(ኢዜአ)፦ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲው በተሳካ ሁኔታ እንዲተገበር የፍትሕ እና የፀጥታ ተቋማት ሚና የላቀ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ገለጹ።

ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ላይ ገለጻ ሰጥተዋል።


 

ኢትዮጵያ ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ በመግባት የለውጥ ምዕራፍ ላይ እንደደረሰች የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ስለ ማሻሻያው ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ማስጨበጥ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ማሻሻውን ለማደናቀፍ ሆን ብለው ሕግ የሚጥሱ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ሚኒስትሩ ማሳሰባቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።


 

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው፤ እየተተገበረ ስላለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ፣ የፖሊስ አመራሩ አስቀድሞ መረጃዎችን ማወቁ ለሕግ ማስከበር ሥራው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም