ቀጥታ፡

በኦሊምፒክ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 7/2016(ኢዜአ)፦በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ።

በፓሪስ በተካሄደው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል።

ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የሚኒስቴሩ የዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮችና ሌሎች እንግዶች አቀባበል አድርገውለታል።


 

ኢትዮጵያ በአትሌቲክስና ውሃ ዋና ስፖርት 38 ስፖርተኞችን አሳትፋለች። 1 የወርቅና 3 የብር አጠቃላይ 4 ሜዳሊያዎችን በማግኘት 47ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

በአትሌቲክስ የሜዳሊያ ሰንጠረዥም 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

በተጨማሪም ለልዑካን ቡድኑ ዛሬ ከሰዓት በብሔራዊ ቤተ መንግስት የእውቅናና የሽልማት መርሐ ግብር ይካሄዳል።

ትናንት ልዑኩ ፓሪስ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሽኝት እንደተደረገለት ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም