ኢትዮጵያና ኩዌት የተፈራረሙትን የስራ ስምሪት ስምምነት ወደ ትግበራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያና ኩዌት የተፈራረሙትን የስራ ስምሪት ስምምነት ወደ ትግበራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2016 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያና ኩዌት የተፈራረሙትን የስራ ስምሪት ስምምነት ወደ ትግበራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ
በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሰኢድ ሙሐመድ (ዶ/ር) ከኩዌት የሰው ኃይል ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ሙሳድ አል-ሙታሪ ጋር በስምምነቱ ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት ማካሄዳቸው ተገልጿል።
አምባሳደር ሰኢድ መንግስት የኢትዮጵያ ዜጎች ወደ ኬዌት ከመምጣታቸው በፊት የሚያስፈልጋቸውን እውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል
የኩዌት የሰው ኃይል ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ሙሳድ አል-ሙታሪ
መንግስታቸው የስራ ስምምነቱ ወደ ትግበራ እንዲገባ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውና ለዚህም አስፈላጊውን ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በስምምነቱ መሰረት የቴክኒካል ኮሚቴ አባላት በፍጥነት ተዋቅሮ ወደ ስራ እንዲገባ የቅርብ ክትትል ይደረጋል ብለዋል።
በውይይቱ ላይ ከሁለቱም አገራት የተውጣጣ ቴክኒካል ኮሚቴ በአጭር ጊዜ ለማቋቋም ከስምምነት ላይ መደረሱን ኢዜአ በኩዌት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።