ቀጥታ፡

የመጀመሪያው ዙር ዓለም አቀፍ የክረምት ነጻ የጤና አገልግሎት ሰጪዎች ቡድን ኢትዮጵያ ገባ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2016 (ኢዜአ)፡-  የመጀመሪያው ዙር አለም አቀፍ የክረምት ነጻ የጤና አገልግሎት ሰጪዎች ቡድን ኢትዮጵያ ገብቷል።

በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ለቡድኑ አቀባበል አድርገውለታል።


 

ቡድኑ 26 ነጻ የጤና አገልግሎት ሰጪ ሕንዳውያን የያዘ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። 

ሕንዳውያኑ በሮተሪ ኢንተርናሽናል የአዲስ አበባ ክለብ፣ በሮተሪ ኢንተርነሽናል ቻንዲጋር ክለብና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ትብብር መምጣታቸውን ገልጿል።

የጤና አገልግሎት ሰጪ ቡድኑ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ፣ በአለርት ሆስፒታልና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከ1 ሺህ 500 በላይ ነጻ የቀዶ ህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

የክረምት በጎ አድራጎት አካል የሆነው ነጻ የጤና ምርመራና ሕክምና አገልግሎት በአገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም የጤና ተቋማት መጀመሩ ይታወቃል።

ከተለያዩ አገራት የክረምት ነጻ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የተለያዩ አገር ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም