ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ የምትጠበቅበት የሴቶች ማራቶን ውድድር ተጀመረ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 5/2016(ኢዜአ)፦ በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለሜዳሊያ የሚጠበቁበት የሴቶች ማራቶን ውድድር በመካሄድ ላይ ነው።

የርቀቱ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት አትሌት ትዕግስት አሰፋ፣ አትሌት አማኔ በሪሶና አትሌት መገርቱ ዓለሙ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ።

በውድድሩ ላይ በቶኪዮ በተካሄደው 32ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችው ኬንያዊቷ አትሌት ፔሬዝ ጄፕቺርቺርና በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ኔዘርላንዳዊ የሆነችው አትሌት ሲፋን ሀሰን የኢትዮጵያ አትሌቶች ዋንኛ ተፎካካሪዎች ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም