ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አትሌቶች በሴቶች 1500 ሜትር ሜዳሊያ ውስጥ መግባት አልቻሉም

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 4/2016 (ኢዜአ)፡- በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በሴቶች የ1500 የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሜዳሊያ ውስጥ መግባት ሳይችሉ ቀርተዋል።

አትሌት ድርቤ ወልተጂ አራተኛና አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 12ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

ኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕዬጎን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም