ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አትሌቶች የሚሳተፉባቸው ሁለት የፍጻሜ ውድድሮች ማምሻውን ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 4/2016(ኢዜአ)፦ በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ አትሌቶች የሚሳተፉባቸው ሁለት የፍጻሜ ውድድሮች ከጥቂት ቆይታ በኋላ ይካሄዳሉ።

ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ላይ በወንዶች 5000 ሜትር ፍጻሜ አትሌት ሐጎስ ገብረሕይወት፣ አትሌት ቢኒያም መሐሪና አትሌት አዲሱ ይሁኔ ይወዳደራሉ።

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይና አትሌት ድርቢ ወልተጂ የሚሳተፉበት የ15000 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ ከምሽቱ 3 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ላይ ይደረጋል።

ኢትዮጵያ በፓሪስ እየተካሄደ ባለው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ዛሬ በወንዶች ማራቶን በአትሌት ታምራት ቶላ ማግኘቷ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም