ለሀገሩ ዋጋ የከፈለ ሠው ማንም ቢሆን የተከበረ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ለሀገሩ ዋጋ የከፈለ ሠው ማንም ቢሆን የተከበረ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 4/2016(ኢዜአ)፦ለሀገሩ ዋጋ የከፈለ ሠው ማንም ቢሆን የተከበረ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የኢትዮጵያ ታሪክ ዋነኛ መሠረቱ ወታደር ነው አይተኬ ህይወቱን ገብሮ ሀገርና ትውልድ ያጸናል፤ ከሠፈርና ከመንደር የተሻገረ የላቀ አላማ እና መስዋዕትነት የያዘ ሠራዊት ሀገርን ይታደጋል ሲሉ አስፍረዋል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት በየደረጃው የገጠመው ፈተና የተሻለ ደረጃና አቅም ያለው ሆኖ ዳግም እንዲፈጠር አስችሎታል፤ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን አቅሙን በመጠቀም በበለጠ ፍቅርና ታማኝነት ሊያገለግል ይገባል ብለዋል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት በለውጥ ንቅናቄ የተጓዘባቸውን መንገዶች በተመለከተ ከመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር የጋራ አረዳድ ለመፍጠር የተዘጋጀው መድረክ የተሳካ ነበር ሲሉም ገልጸዋል።