ቀጥታ፡

በሐረሪ ክልል ለአገራዊ ምክክር ግብዓት የሚሆን አጀንዳ ማሰባሰቢያ የቡድን ውይይት ተጀመረ

ሐረር፤  ነሐሴ 4/2016 (ኢዜአ) ፡- በሐረሪ ክልል ለአገራዊ ምክክር ግብዓት የሚሆን አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት በቡድኖች ተለይቶ ውይይት ዛሬ መካሄድ ጀመረ።

በኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም ከበደ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሐረሪ ክልል  አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ተጀምሯል።


 

ውይይቱ ከሰዓት በኋላ በ10 የማህበረሰብ ቡድኖች ተለይተው ውይይት እያካሄዱ  መሆኑን አስታውቀዋል።

በክልሉ ከሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች የተውጣጡ 360 ተወካዮች በቡድን ውይይቱ እየተሳተፉ መሆኑንም ኃላፊው ገልጸዋል።

ውይይቱ በአርሶ አደሮች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ መምህራን፣ መንግስት ሠራተኞች፣ እድሮች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ በተፈናቃዮች፣ በታዋቂ ሰዎችና በሌሎችመ  የህብረተሰብ ክፍሎች ተለይቶ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

እያንዳንዱ የማህበረሰብ የውይይት ቡድን አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራውን የጀመረው አሳታፊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የየራሱን ሰብሳቢ እና ፀሐፊ በመምረጥ እንደሆነም አቶ አብርሃም አስታውቀዋል።

የማህበረሰብ ቡድኖች እስከ ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ለአገራዊ ምክክሩ ከተወከሉበት ማህበረሰብ ያመጡትን አጀንዳ አጠቃለው ለኮሚሽኑ እንደሚያስረክቡ ኃላፊው  አስረድተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም