ቀጥታ፡

በልምምድ ላይ የነበረ ቀላል አውሮፕላን ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር በድንገት ለማረፍ ተገዷል -የኢትዮጵያ አየር መንገድ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 4/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የሐዋሳ ቅርንጫፍ በመደበኛው የፓይለት ስልጠና ልምምድ ላይ የነበረ ቀላል የተማሪዎች መለማመጃ አውሮፕላን (Dimond DA40NG) አየር ላይ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት አርሲ ነጌሌ አካባቢ ለማረፍ መገደዱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ።

አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ እንደገለጸው ይህንን ተከትሎ በመደበኛ ስልጠናው ላይ የነበሩት አስተማሪውና ተማሪው የመለማመጃ አውሮፕላኑን ሕብረተሰቡ ላይ አደጋ በማያደርስ ሁኔታ ለማሳረፍ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።

ሆኖም ለማረፍ በተደረገው ጥረት መሬት ላይ በነበረች አንዲት ታዳጊ ላይ ጉዳት መድረሱን በመግለጽ ለተፈጠረው ሁሉ እያዘንን ለታዳጊዋ ቤተሰቦች ፍፁም መፅናናትን እንመኛለን ብሏል።

የአደጋው መንስኤ በሚመለከታቸው አካላት በመጣራት ላይ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን ሲልም አየር መንገዱ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም