ቀጥታ፡

አትሌት ታምራት ቶላ የመጀመሪያውን የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኘ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 4/2016(ኢዜአ)፦በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በወንዶች ማራቶን የፍጻሜ ውድድር አትሌት ታምራት ቶላ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

ታምራት 2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ26 ሴኮንድ በርቀቱ የኦሊምፒክ ክብረ ወሰንን አሻሽሏል።

አትሌት ደሬሳ ገለታ አምስተኛና አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 39ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም