የሀይል መሰረተ ልማቶችን የማሻሻል ሂደት ላይ ሁዋዌ እንዲሳተፍ እንፈልጋለን - ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር ኢ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የሀይል መሰረተ ልማቶችን የማሻሻል ሂደት ላይ ሁዋዌ እንዲሳተፍ እንፈልጋለን - ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር ኢ/ር)
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 3/2016(ኢዜአ)፦የሀይል መሰረተ ልማቶችን የማሻሻልና የማዘመን ሂደት ላይ ሁዋዊ ተሳትፎ እንዲያደርግ የውሃና ኤነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ጠየቁ።
ሚኒስትሩ ከሁዋዌ የምስራቅና መካከለኛው የአፍሪካ ቀጣና ፕሬዝዳንት ሚስተር ጀሪ ቼን ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም ሁዋዌ ያለውን ልምድና አቅም በመጠቀም በኢትዮጵያ የውሃ ሀብት መረጃ አስተዳደርን ለማዘመን የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዝ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል፡፡
በመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን አገልግሎት የማዘመን ስራ እና በኢነርጂ ልማት ዘርፍ እየተደረገ በሚገኘውን የአውቶሜሽን ትግበራ ላይ ከኩባንያው ጋር በትብብር እንደሚሠሩም ጠቁመዋል።
የኃይል መሰረተ ልማቶችን የማሻሻልና የማዘመን ሂደት ላይም ኩባንያው ተሳትፎ እንዲያደርግ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል።
እንዲሁም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ከማበረታታት አንጻር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል መሙያ ጣቢያችዎችን ለማስፋፋት እንዲሠሩም መጠየቃቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።