የአካል ጉዳተኞች መብቶች፣ ጥቅሞችና ተሳትፎ ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ መጠናከር እንዳለበት ተመለከተ - ኢዜአ አማርኛ
የአካል ጉዳተኞች መብቶች፣ ጥቅሞችና ተሳትፎ ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ መጠናከር እንዳለበት ተመለከተ
አዳማ፤፤ ነሐሴ 3/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች መብቶች፣ ጥቅሞችና ተሳትፎን ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ መጠናከር እንዳለበት ተመለከተ።
ዛሬ በአዳማ ከተማ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን 'አፍሪካ አካል ጉዳኞች ፕሮቶኮል' የተመለከተ ገለጻ ለፌዴሬሽኑ የስራ አመራር ቦርድ አባላትና ሚዲያ አካላት ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
ፕሮቶኮሉ የተጠቃለለ የአካል ጉዳተኞች መብቶችና ጥቅሞች የሚያስጠብቁ ህጎች ያካተተ መሆኑም ተመልክቷል።
በማብራሪያው የአካል ጉዳተኞች መብቶች፣ ጥቅሞችና ተሳትፎ በመሰረታዊነት ማሻሻል የሚያስችል የተጠቃለለ የአካል ጉዳተኞች ህግ እንዲጸድቅ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ጉጆ እንደተናገሩት፤ ፕሮቶኮሉ ጸድቆ እንዲተገበርና የአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ መብቶች እንዲረጋገጡ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ማደግ አለበት።
በፕሮቶኮሉ ይዘት ዙሪያ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት ተፈጻሚነቱን ለማፋጠን ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሳልፈው አህመዲን በበኩላቸው፤ ፕሮቶኮሉ አካል ጉዳተኞችን የተመለከቱ ሁሉንም መብቶች ያካተተ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዚህም ከአካል ጉዳተኞች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ምርምሮች፣ የመገልገያ መሳያዎች፣ ለቅንጅትና ለትብብር የሚያግዝ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ይኸውም በአካል ጉዳተኞች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ዙሪያ መሰረታዊ ለውጥ እንዲመጣ የታለመ ነው ብለዋል፡፡