የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት “የፕሬዚዳንቱ የሕይወት ዘመን ሽልማት” ተበረከተለት - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት “የፕሬዚዳንቱ የሕይወት ዘመን ሽልማት” ተበረከተለት
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 2/2016(ኢዜአ)፦ በአፍሪካ አቪዬሽን ዘርፍ ቀዳሚና ስኬታማ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት “የፕሬዚዳንቱ የሕይወት ዘመን ሽልማት” ተበርክቶለታል።
ይህ ሽልማት በአሜረካ ውስጥ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ለተሰጠ የላቀ አገልግሎት ዕውቅና የሚሰጥ ሲሆን በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላበረከተው ዘርፈ ብዙ አስተዋፅዖ ይህ ሽልማት ሊበረከትለት መቻሉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ ያመለክታል።
በአለም ላይ በፍጥነት በማስፋፋት ላይ የሚገኘው አየር መንገዱ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፊርማ ያረፈበትን ሽልማት የተቀበለ ሲሆን ሽልማቱም የተበረከተው 8ኛው አመታዊ የጥቁሮች ማህበር ባዘጋጀው የእራት ዝግጅት ላይ ነው።